ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን በጋራ በተባባረ ክንድ በጽናት ተግዳሮቶችን በመቋቋም ጣፋጭ ድልና ስኬቶችን ማስመዝገብ ችሏል፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)




ኢትዮጵያውያን በጋራ በተባባረ ክንድ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በጽናት ተቋቁሞ ጣፋጭ ድልና ስኬቶችን መቀዳጀት ችሏል ስሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተደድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገልጿል።
በክልሉ እየተከበረ ያለዉን የጳጉሜ 01 ቀን አስመልክቶ መልዕክት የክልል ርዕሰ መስተደድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እኛ ኢትዮጵያውያን በህብረ ብሔራዊ አንድነትና ትብብር ስንቆም የማንወጣው ዳገትና የማንሻገረው አንድም ፈተና የለም ብለዋል።
በዚህም በታላቁ በህዳሴ ግድብ ያየነውን ትብብርና የተቋቋምነው መሰናክል የፈጠርናቸው አንድነትና ያስገኘነው ጣፋጭ ድል ባለፉት መቶ አመታት ውስጥ ከገኘነው ድል የላቀ ታላቅ ድል እንደሆነ ገልጸዋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘመናት መካከል እንደ ሀገር፣እንደ መንግስት በርካታ ፈተናዎችን ተቋቁማ በድልና በፅናት እየተሻገረች ትገኛለች ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም ለዛሬው ጣፋጭ ድል አብቅቶናል ብለዋል።
ህብረ ብሔራዊ አንድነት ፣ወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር የሚገጥሙን ፈተናዎች ጊዜያዊ መሆናቸውን በውል በመገንዘብ እጅ ለእጅ ተያይዘን የጀመርነውን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ለማድረግ የበረታን ሆነን መገኘት አለብን ብለዋል።
የኢትዮጵያውያን የቁጭትና የላብ ውጤት የሆነው ህዳሴ ግድብ የፅናት ተምሳሌታችን መሆኑን አብራርተዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
