“በሁሉም አካባቢ የሚኖረውን ህዝባችንን ፈተናዎች እና ፍላጎቶች ማዳመጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው”፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)::

Spread the love

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በሁሉም አካባቢ የሚኖረውን ህዝባችንን ፈተናዎች እና ፍላጎቶች ማዳመጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው” ሲሉ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ፤ከደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሲዳማ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

በውይይቱም ተወካዮች በልማት ጉዳዮች ላይ አስተያየቶቻቸውን እና ጥያቄዎቻቸውን ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጋራ ግብ ላይ ለመድረስ የኅብረትን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተው ምላሽ መስጠታቸው ተጠቅሷል።

ኢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *