በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ የህዝብ የልማት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መጠነ ሰፊ ተግባራት ተከናውኗል። አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፓርላማ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤት አባላት የክረምት ወራት የውክልና ስራዎች ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ አቶ ወንድሙ ኩርታ፥ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት በክልሉ የህዝብ የልማት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መጠነ ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።
ለተመዘገበው ሁለንተናዊ ለውጥ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ክትትልና ድጋፍ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ያሉት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ የመጡ አውንታዊ ለውጦች በማስቀጠል በቀጣይ ለተሻለ አፈጻጸም መትጋት ይገባል ብለዋል።
የፓርላማ ተወካዮች ከክልል ምክር ቤት አባላት ጋር በመቀናጀት በክረምት ወራት በየዞኑ በሚያከናውኑት የውክልና ስራዎች ስትራቴጂካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማተኮር እንደሚገባም አቶ ወንድሙ ተናግረዋል።
የምክር ቤቱ አባላት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን በዝርዝር በመቃኘት እንደ ክልል ምላሽ የሚሹ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በመለየት ለክልሉ መንግሥት ግብረ-መልስ መስጠት እንደሚገባም ጨምረው ገልጸዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የበድኑ መሪ የተከበሩ አቶ ዳውድ መሀመድ በበኩላቸው፥ ባለፈው ጊዜ ከመራጩ ህዝብ ጋር በተፈጠረው መድረክ የተነሱ የልማት ጥያቄዎችን በሚመለከት ከአስፈጻሚ ተቋማት ጋር በተገቢው መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።
በዚህም የተገኙ ውጤቶችን በመገምገም በመቀጣይ ምላሽ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ለመመካከር የክረምት ወራት የውክልና ስራ የጎላ አበርክተው እንዳለውም አቶ ዳውድ ገልጸዋል።
በዞኖች በሚኖረው መድረክ ባለፉት ጊዜያት በህዝቡ ዘንድ የተነሱ ጥያቄዎችና የተሰጡ ምላሾችን ለህዝብ በመግለጽ በቀጣይ ስራዎች ላይ የጋራ መግባባት የሚፈጠርበት እንደሆነም አቶ ዳውድ ጨምሮ ተናግረዋል።
የመድረኩ ተሳታፊ የፓርላማ እና የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፥ በታችኛው መዋቅር በሚፈጠረው መድረክ ሁሉም የህዝብ ተወካዮች በየምርጫ ክልላቸው በመገኘት የህዝባቸውን ጥያቄዎችን ማድመጥ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
በምክክርና ኦረንቴሽን መድረኩ የፓርላማ አባላት እና የክልል ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
