የኢትዮጵያ ስነ ልክ ኢንስቲትዩትግምታቸው ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የስነ ልኬት መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ



ድጋፍ የተደረጉት የስነ ልኬት መሳሪያዎች ህገወጥ ንግድን ለመከላከል ያግዛልም ተብሏል።
የኢትዮጵያ ስነ ልክ ኢንስቲትዩት ግምታቸው ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የስነ ልኬት መሳሪያዎችን ለክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ድጋፍ አድርጓል ።
በኢንስቲትዩቱ የመሠረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ሙሉነህ የነዳጅ፣የጠረጴዛና የምድር ኪሎ ስታንዳርድ መለኪያ መሳሪያዎች በድጋፍ መሰጠታቸውን በርክክቡ ወቅት ገልጸዋል።
የተደረገው ድጋፍ እየተስተዋለ ያለውን ህገወጥ የንግድ ግብይትን ለመቆጣጠርና ስታንዳርድ አገልግሎት አሰጣጥን ለማረጋገጥ ያግዛልም ሲሉ አቶ ሙሉነህ ተናግረዋል ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ የንግድ ሬጉሌሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ አበበ አስፋው የተደረገው ድጋፍ በንግድ ግብይት ወቅት እየተስተዋለ ያለውን የተዛባ የሚዛን አጠቃቀምን ለማረም የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል ።
በድጋፍ የቀረቡት የስነ ልኬት መሳሪያዎች በነዳጅ ግብይት፣በሸቀጣ ሸቀጦች ንግድ ላይ ስታንዳርዱን የጠበቀ አገልግሎት ስለመሰቱ የሚረጋገጥበትና ሸማቹ ማህበረሰብ በትክክለኛ ሚዛን ግብይት እንዲፈጽም የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ስነ ልክ ኢንስቲትዩት ለክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ላበረከተው ድጋፍም አቶ አበበ በቢሮው ስም አመስግነዋል ።
በታጠቅ አበበ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
