በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በፓርቲ መሪነት የተከናወኑ ተግባራት ውጤቱ የሚመዘን ለመጪው ሥራ መነሳሳትን የሚፈጥርና ለተልዕኮዎቹ ጠንካራ መሠረት የጣለ መሆኑ ተመላከተ

Spread the love

በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቤት በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የግምገማ መድረክ ቀጥሏል።

በግምገማ መድረኩ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በበጀት ዓመቱ በጥንካሬ የተመዘገቡትን ማጠናከር እና ጉድለቶችን ማሻሻል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስቷል።

በበጀት ዓመቱ በፖለቲካና አቅም ግንባታ፣በአደረጃጀት ፣ዴሞክራሲ ባህል ግንባታ፣ህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ፣በሀብት አስተዳደር፣ወጣቶችና ሴቶች ክንፍ እንዲሁም በንቅናቄ የሚመሩ አጀንዳዎች ከሌሎች ዓመታት በተሻለ ውጤቶች መመዝገባቸው ተገልጿል።

በፓርቲው መሪነት የሚከናወኑ የመደበኛ እና የንቅናቄ አጀንዳዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ በማከናወን የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚጠበቅም የመድረኩ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን ሰጥቷል።

በበጀት ዓመቱ በንቅናቄ የሚመሩ የኢንሼቲቭ አጀንዳዎች በተለይም የሌማት ትሩፋት፣የከተማና ገጠር ኮሪደር ልማት፣ትምህርት ለትውልድ፣ጤና መድህን አገልግሎትና ሌሎች የጤና ልማት ሥራዎችና አገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን እና በማቀላጠፍ ረገድ የተጀመሩ ሥራዎችን ማጠናከር ያስፈልጋልም ብለዋል።

ሌብነትና ብልሹ አሰራር መዋጋት እና ለመልካም አስተዳደር ችግር ምንጩ ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን መፈተሽና ማራም ያስፈልጋል ያሉት ተሳታፊዎች የአደረጃጀት ሥራዎች የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ተግባራቶችን ከተለመደው አሰራር ወጥቶ ወጥነት ባለዉ መልኩ ማከናወን እንደሚገባ ነዉ ያመላከቱት።

በሀብት አስተዳደር እና አሰባሰብ ላይ ትኩረት ማድረግ፣የሴቶችና ወጣቶችን ክንፍ አደረጃጀት ማጠናከር፣ በአላማ የጸና፣በአመለካከትና በአስተሳሰብ የጠራ ብሎም በፈተና የማይበገር የብልጽግና ቤተሰብ በመፍጠር ረገድ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል አለባቸዉም ብለዋል።

የመጣው አንጻራዊ ሠላም ወደ ዘላቂ እንዲሸጋገር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር፣እርቀ ሰላም ማውረድ፣ስጋት ቀጠናዎችን መለየትና ችግሮችን ለይቶ መፍታት ይገባልም ብለዋል።

ከተረጂነት መላቀቅ የሚያስችል ምርትና ምርታማነት ማሳደግ፣ለሚያጋጥሙ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት ብሎም ወጭን በራስ አቅም መሸፈን እንዲያስችል አስተማማኝ ሀብት በፓርቲ መሪነት ማሰባሰብ እንደሚገባ ነው ተሳታፊዎች ያነሱት።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ በወቅቱ እንደገለጹት በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በፓርቲ መሪነት የተከናወኑ ተግባራት ውጤቱ የሚመዘን መነሳሳትን የሚፈጥርና ለመጪው ተልዕኮ ጠንካራ መሠረት የጣለ ነው ብለዋል።

የተመዘገበዉ ውጤት ከእቅድ ጀምሮ የተጠናከረ ቅንጅትና ትብብር እንዲሁም ርብርብ መደረግ በመቻሉ ነው ያሉት አቶ ነጋ አበራ ብልጽግናን በቤተሰብ ደረጃ ማረጋገጥና ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበ የመፈጸም እና ማስፈፀም አቅም ማጠናከር ሥራዎች ተጠናክሮ ይቀጥላሉም ብለዋል።

ፓርቲው ጠንካራ እንዲሆን በየደረጃው አደረጃጀቶችን ማጠናከር ቁመናን መፈተሽ በመደበኛነት እና በንቅናቄ የሚመሩ አጀንዳዎችን በተገቢው መፈጸምና ማስፈጸም እንደሚያስፈልግ የተናገሩት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ ናቸዉ።

ከ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም መነሻ ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው ጠንካራ ፓርቲና መንግስት መገንባት እንዲቻል ከክልል እስከታችኛው መዋቅር በመደበኛነት እና በንቅናቄ የሚመሩ ጉዳዮችን ብልጽግናን ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ማከናወን ይገባል ብለዋል።

በተቋማት የመንግስትና የፓርቲ ተልዕኮችን በተገቢው ማቀድ፣መፈጸምና ተግባራትን መከታተል የሚችል አመራር መፍጠር ይጠበቃል ያሉት አቶ ፍቅሬ ህብረብሔራዊ አንድነት ማጠናከርና የህዝቡ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ማዳመጥና ፈጣን ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥቷል።

የሚዲያ አጠቃቀም ማሻሻል፣በከተማም ሆነ በገጠር የሚከናወኑ የንቅናቄ አጀንዳዎችን በልዩ ትኩረት መምራት፣ሰላም በተረጋገጡ አከባቢዎች ህዝቡ ወደ ልማት እንዲገባ ማስቻል ይገባል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *