የሸካቾ ብሔረሰብ የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም በጌጫ ከተማ መካሄድ ጀምሯል

Spread the love

ማሽቃሬ ባሮ ትናንትን ከነገ፤ባህልን ከልማት”በሚል መሪ ቃል የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም በሸካ ዞን ምሁራን ማህበር አዘጋጅነት በጌጫ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

የፓናል ውይይትና ሲምፖዚየሙ በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት ነው የተጀመረው።

የሸካቾ ብሔረሰብ ቋንቋ ያለበትን የእድገት ደረጃና ተግዳሮቶች ላይ ውይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ተጠቁሟል።

የሸካቾ ብሔረሰብ ለሀገር የሚተርፍ ሀገር በቀል እውቀትና ባህል ያለው በመሆኑ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርበው በምሁራኑና የሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

በሲምፖዚየሙ ላይ የሸካ ንጉስ ተቺ ቄጆቺና ምክረቾዎቻቸው፣የብሔረሰቡ ተወላጆችና ወዳጆች፣ የፌዴራልና ክልል ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ፣የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *