በ2018 በጀት ዓመት በህልና፣አስተሳሰብ እና በተግባር አንድ በመሆን ከሌሎች ጊዜያት በተሻለ ተልዕኮችን መፈጸም እንደሚገባ አቶ ፍቅሬ አማን አሳሰቡ።

Spread the love

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቤት በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በሚዛን አማን ከተማ የሚያካሂደዉ የግምገማ መድረክ ተጠናቀቀ

‎በመድረኩ ያለፈው 2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ከመገምገም ባሻገር 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ በመወያየት የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

‎የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንደተናገሩት፤እስካሁን ከመጣንበት ይልቅ ቀጣይ የሚንጓዘዉ ርቀት ውስብስብ እና ፈታኝ ድርብርብ ተልዕኮዎች የሚጠብቁብን ወቅት ላይ እንገኛለን።

‎ቀጣይ የሚጠብቁብን በርካታ ተልዕኮችን መፈጸም እንዲቻል የአመራሩ እና አባላት የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት በየጊዜው መፍተሽና መገምገም እንደሚገባ ነው አቶ ፍቅሬ አማን ያስገነዘቡት።

‎በተቋማት፣በአስፈፃሚዎችና በፈጻሚዎች ደረጃ ውጤታማነትን እያረጋገጡ መሄድ ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ፍቅሬ ለጠንካራ መንግስት ግንባታ ጠንካራ ፓርቲ መገንባት ወሳኝ ጉዳይ ነውም ብለዋል።

‎በፓርቲው መሪነት የሚወርዱ የኢንሼቲቭ አጀንዳዎችን መከታተልና ውጤታማነቱን መፈተሽ የህዝብን ተሳትፎ ማጠናከርና የህዝቡ የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

‎በተያዘዉ 2018 በጀት ዓመት በህልና፣አስተሳሰብ እና በተግባር አንድ በመሆን ከሌሎች ጊዜያት በተሻለ ተልዕኮችን መፈጸም እንደሚገባም አቶ ፍቅሬ አማን አሳስበዋል።

‎በመድረኩ ማጠቃለያ በክልሉ በሁሉም ዞን መዋቅሮች

‎በሚገነባው የፓርቲ ጽ/ቤት ህንጻ ግንባታ ዙሪያ ውይይት ተደርገው የግብ ስምምነት ተፈጽሟል።

‎በተጨማሪም በ2017 በጀት ዓመት በተለያዬ መመዘናዎች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዞኖች እውቅና እና ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

‎የተሰጠው እውቅና እና ማበረታቻ ለቀጣይ ተልዕኮ መነሳሳትን የሚፈጥር፣ተቀራራቢ ውጤት ለማስመዝገብ ጤናማ ፉክክር የሚያሳድር እንዲሁም የተግባራትን ውጤታማነት የሚያሳድግ መሆኑም ተመላክቷል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *