
ዋና አፈጉባኤ ወንድሙ ኩርታ የቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” መከበሩ ክልሉ ለባህል መጎልበት የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው ብለዋል።
የክልሉ መንግስት የብሔሮች ብሔረሰቦች ባህል ጎልቶ እንዲወጣ፣እንዲለማና ጥቅም ላይ እንዲውል በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል በመልዕክታቸው ።
የቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” ቀደምት አባቶች ያቆዩትና በመሀልም ተረስቶ ለዘመናት ሳይከበር እንደቆየም አስታውሰዉ አሁን በደመቀ መንገድ መከበሩ ይህንን አኩሪ ባህል ለማሳደግ ስራ ስለመጀመሩ ማሳያ ነዉ ብለዋል።
የአሁኑ ትውልድ ይህንን ዕሴት በጥናት ለመመለስ ያደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው ያሉት ዋና አፈጉባዔ ወንድሙ ኩርታ ይበልጥ ለምቶ ጥቅም ላይ እንዲውል የክልሉ ምክር ቤት ያግዛል ብለዋል።
በክልላችን የሚገኙ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባህላዊ እሴቶቻቸው እንዲለሙና ጥቅም ላይ እንዲውሉም የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል ።
በዓሉ የፍቅር፣የአንድነትና የመተሳሰብ እንዲሆንም አፈጉባኤ ወንድሙ ኩርታ ተመኝተዋል።
መልካም “ቢስት ባር “
