




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ”ከቃል እስከ ባህል”በሚል መሪ ቃል በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።
ውይይቱ በጉባዔው በተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ትግበራ ለመግባት ዓላማ ያደረገ ነው።
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ብልጽግና ባለፉት ጥቅት ዓመታት የገመጡትን ፈተናዎች በመሸጋገር የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ በርካታ ውጤቶችን ማስመዝገብ የቻለ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ፓርቲው በመጀመሪያው መደበኛ ጉባኤ ያስተላለፋቸው አንኳር ጉዳዮች እስከ ሁለተኛ ጉባኤ በገባው ቃል መሠረት በመፈጸም የህዝቡን የሰላም፣የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ማረጋገጥ ችሏል ስሉ ተናግረዋል ።
በዚህም ሀገሪቱ የገጠማትን የኢኮኖሚው ስብረት መጠገን የሚያስችሉ ፖሊሲ እና ሪፎርም ተግባራዊ በማድረግ በግብርናው፣በቱሪዝም፣ኢንዱስትሪና በሌሎች ዘርፎች ትኩረት አድርጎ መስራቱንም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
ፓርቲው በማህበራዊ ዘርፍ በጤና እና በትምህርት እንዲሁም በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች የሚያጋጥሙ ችግሮችን ከመፍታት ባሻገር የባህር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለማግኘት የሄደበት አካሄድ ለቀጣይ ለብልጽግና ጉዞ ምቹ ምቹ መደላድል እየፈጠረ ይገኛል ነው ያሉት።
ዶክተር ነጋሽ ዋጌሾ በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች እንዲሳኩ አመራሩና አባሉ በወጥነት ተግባሩን ማከናወን እንደሚኖርበትም በአጽንኦት ተናግረዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባልና የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች እንዲሳኩ አመራሩ ፣አባሉና ህዝቡ ከፓርቲው ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
በውይይት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።
በፍቅር ከበደ
