




የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም በደቡብ ምዕራብ ክልል በቦንጋ ከተማ ከክልልና ዞን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በዲጂታል መታወቂያ የ2018 ዓም የፋይዳ ምዝገባ ዕቅድ እና የክልሉ አሁናዊ የምዝገባ ሂዳት ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
የዉይይት መድረኩን የመሩት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንዳሉትር፣በ2018 ዓም ለመፈጸም የተያዘዉን የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ዕቅድን ለማሳካት ከመደበኛ ተግባር ባለፈ በንቅናቄ ስራ የተያዘዉን ዕቅድ ለማሳካት በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል፡፡
ዲጂታል መታወቂያዉ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸዉን አገልግሎቶችን ለማዘመን ያለዉ ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ህብረተሰቡ የፋይዳን አስፈላጊነት ተገንዝቦ እንዲመዘገብ በክልሉ ያለዉን ተቋማት ማስተሳሰርና የአመራሩ የጋራ ጥረት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በበኩላቸው፥ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ሁሉንም የሚያካትት መርሃግብር መሆኑን ጠቅሰዋል።
የተያዘዉን ዕቅድ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ከግብ ለማድረስ የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልጿል፡፡
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ክፍል ሃላፊ አቶ ሄኖክ ጥላሁን በበኩላቸዉ፤በ2018 ዓም የተሻሻለ ሀገር አቀፍ የፋይይ ምዝገባ ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ ያለዉን የመመዝገቢያ ግብዓት(ኪት)ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ፣አፈጻጸሞችን ክትትል የሚያደርግ ባለሙያ የመመደብ እንዲሁም በቴክኒካል ስራዎች ላይ ስልጠና በመስጠት አስፈላጊ ድጋፍ እንደሚደረግም አስረድተዋል፡፡
በመድረኩ ለዕቅድ አፈጻጸም እንደችግር የተነሱ ነጥቦች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት በክልል ደረጃ ለምዝገባዉ የተያዘዉን ዕቅድ ከዳር ማድረስ እንደሚገባ አብራርተዉ የክልሉ አመራር እያደረገ ያለዉ ድጋፍ እና ቁርጠኝነት የሚመሰገን ነዉ ብለዋል፡፡
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ ፋይዳ መንግስታዊ ካርድ ህትመት ከመደረጉ በፊት በጥንቃቄ መስራት እንደሚገባ ገልጸዉ የመረጃ መስተካከያ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ማስተካከያ የሚደረግበት አሰራር መኖሩንም ተናግረዋል፡፡
ከዉይይቱ በርካታ የመረጃ ግብዓት መገኘቱን በመግለጽ ይህ የተያዘዉን ዕቅድ ስኬታማ በማድረግ ሀገራችን ለያዘችው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ስኬታማነት ቁልፍ ሚናን የሚጫወት እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሰጠዉ አመራርና ለተገኘዉ ዉጤት ምስጋና ከፕሮግራሙ ጽ/ቤት ዕውቅና ተሰጥቷል።
በካሳሁን አሰፋ
