7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዳኞች ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Spread the love

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዳኞች ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ አሳስበዋል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር ከምርጫ ጉዳዮች ጋር በተያያዙ በሚመጡ ቅሬታዎች የአፈታት ዘዴ ላይ ለፌደራል እና ለክልል ዳኞች ስልጠና እየሰጠ ነው።

ምርጫው ነፃ እና ገለልተኛ እንዲሆን ተቋማዊ ነፃነት እንዲሁም የዳኞች ብቃት እና ታማኝነት አስፈላጊ በመሆኑ ለዳኞች ተከታታይ ስልጠናዎች ይሰጣሉ ያሉት ደግሞ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተዎድሮስ ምህረት ናቸው።

ዜጎች የመመረጥ እና የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙ ፍርድ ቤቶች ነፃ ሆነው የዜጎችን መብት ለማስከበር እንደሚሰሩ ፕሬዚዳንቱ አረጋግጠዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *