ስልጠናው የአመራሩን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ከመገንባት ባሻገር ሀገራችንና ክልላችን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ትልቅ ስንቅ የተያዘበት መድረክ ነው ፦አቶ ማስረሻ በላቸው

Spread the love

‎”ከመልካም አመራርነት ወደ ታላቅ አመራርነት መሻገር ” በሚል መሪ ቃል ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመተባበር ባለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ስሰጥ የቆየው የአመራር ስልጠና መድረክ ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁነትና ቁርጠኝነት በመፍጠር በስኬት ተጠናቋል።

‎የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ስልጠናው መሠረታዊ የህይዎት ክህሎት ላይ ትልቅ ፋይዳ ያለውና የአመራሩን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን የሚገነባ መሆኑን ገልጸዋል።

‎ስልጠናው አመራሩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በራስ አቅም ለመፍታት እንዲሰራ አቅም የሚፈጥር መሆኑን የጠቀሱት አቶ ማስረሻ የብልጽግና ጉዞን አውን ለማድረግ የበረታን ሁነን መገኘትን ጊዜው ይጠበቃል ብለዋል።

አመራሩ ክልላዊ አንድነትን በማጠናከር፣ወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴቶችን ይበልጥ በማዳበር በክልሉ ያሉትን ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴዎችን በአንድ መንፈስ በማሳለጥ ህዝብንና ሀገርን ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሻገር ከምንጊዜውም በላይ መትጋት ይጠበቃል ብለዋል።

‎ከስልጠና የተገኘውን እውቀትና ክህሎትን በአግባቡ መተግበር ከቻልን በቤተሰ፣በክልልና በሀገር ደረጃ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ተናግረዋል።

‎በቀጣይ የፓርቲና የመንግስት ድርብ ተልዕኮዎችን በአዲስ አስተሳሰብ፣ በፍጥነትና በጥራት ለማሳካት፣ ከመቼውም በላይ ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ብርቱ ትግል ማድረግ ይገባል ሲሉ ጠቁመዋል።

‎ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋጥ በሚደርገው ጥረት የአመራሩ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት ወሳኝ መሆኑንም የገለጹት አቶ ማስረሻ ጊዜን ፣ እዉቀትን፣ ጉልበትን፣ ፀጋዎችን ፣ የሕዝብ ዐቅሞችን፣ የመልማት እምቅ ዕድሎችን አቀናጂቶና አስተባብሮ በመምራት የብልጽግና ጉዞን ማፋጠን መቻል ይጠበቃል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *