በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ በመፍታት ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ የካፋ ዞን አስተዳደር ጥሪ አቀረበ

Spread the love

የዞኑ ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ግምገማ ነክ የንቅናቄ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡

በመክፈቻው ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በዞኑ ያሉ አቅሞች በመለየት በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ማነቆዎች በመፍታት ምርትና ምርታማነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ልሰሩ እንደሚገባ አሳሰበዋል፡፡

የመምሪያው ሀላፊ አቶ ጋዎ አባመጫ በበኩላቸው በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በመደበኛ መሰኖ፣ በልግ ተግባራት፣ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት እና ሌማት ቱሩፋት ለውጦች እየተመዘገበ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የግብርና ልማት ግኑኝነት አማካሪ ካውንስል

ምርምር፣ ኢንስፔክሽን አርሶ አደሩን የሚያስተሳስር መሆኑን ገልጸው ለተግባራዊነቱ ሁሉ የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

የመምሪያው ምክትል ሀላፊና የእርሻና ህብረት ስራ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አክሊሉ አማደ በበጀት ዓመቱ ባለሀብቶችን፣ ወጣቶችንና አርሶ አደሩን በማስተባበር 3 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት 120 ሺህ ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን 9 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡

ጠባቂነት፣ ትራክተሮች ወደ ስራ አለመግባት፣

አርሶ አደሩ የግንዛቤ ክፍተት መኖር፣ አሲዳማነት፣ የግብርና ስራ በተቀመጠው ልክ አለመመራትና ህገ ውጥነት መበራከት ተግዳሮቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ የቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል ተመራማሪዎች ጥናታዊ ጽሁፎችን አቅርበዋል፡፡

የ2016/17 ምርት ዘመን ሪፖርት በባለድርሻ አካላት የቀረበ ሲሆን የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየት ተነስተው ምላሸና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የሺሾእንዴ ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አዱኛ ዓለሙ እና የጊምቦ ወረዳ ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰለሞን መንገሻ በየወረዳቸው የግብርና ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

በመድረኩ በዞኑ የሚገኙ የሁሉም ወረዳዎች አስተዳዳሪዎች፣ የግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሞያዎችና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *