






ለቅርንጫፉ መከፈት ከፍተኛውን ድርሻ ለተወጡ አካላት በሙሉ ሸካ ዞን አስተዳደር ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል።
ከኢፌዲሪ ቡናና ሻይ ባለስልጣን እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡናና ሻይ ባለስልጣን የተውጣጣ የአመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ቡድን በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ተገኝተው የቡና ቅምሻ ላቦራቶሪና ሠርተፊኬሽን ማዕከልን በቴፒ ከተማ ለመክፈት እየተደረገ ያለውን ዝግጅት ምልከታ አድርገዋል።
የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ለቡድኑ እስካሁን የተደረሰበትን ተግባር በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን በቀጣይ አጭር ቀናት የላቦራቶሪና የቢሮ ቁሳቁሶችን አሟልተን በአጭር ጊዜ ሥራውን ለማስጀመር ዝግጁ ነን ብለው ለዚህም የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ ዝግጁ እንደሆኑም አንስተዋል።
ከኢፌዲሪ ቡናና ሻይ እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡናና ሻይ ባለስልጣን የተውጣጣ የአመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ቡድን በመስክ ምልከታው የቢሮና ላቦራቶሪ ክፍሎችን የጎበኙ ሲሆን ከነማስተካከያው የተዘጋጀው ቢሮ ለሥራው ምቹ እንደሆነ ገልፀዋል።
እስካሁን የተሠሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸው በተሠጠው አስተያየት መሠረት በአጭር ጊዜ ቀሪ ተግባራትን በማጠናቀቅ ለሥራ ዝግጁ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ገልፀው የቴፒ ቡና ላቦራቶሪ እና ቅምሻ ማዕከልን በፍጥነት ወደ ስራ ለማስገባት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል።
