

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ገና ከአልጄሪያ አቻቸው ሙስተፍ ሂደዊ ጋር ተወያይተዋል።
ፕሬዝዳንቶቹ ከአራተኛው የፓን አፍሪካ የወጣቶች ጉባኤ ጎን ለጎን ነው የሁለትዮሽ ውይይት ያካሄዱት።
በውይይታቸውም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በወጣት ፕሮግራሞች ልውውጥ በጋራ ለመስራት መምከራቸው ተገልጿል።
ፕሬዝዳንቶቹ የወጣቶች የድንበር ተሻጋሪ በጎፈቃድ አገልግሎትን ለማስጀመር ከስምምነት መድረሳቸውም ተመላክቷል።
ከስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች ወደ ስራ ለማስገባትና የመግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም የሚያስችል የቴክኒክ ቡድን መቋቋሙን የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
