በክልሉ የዘንድሮ በልግ ምርት ዘመን ሥራዎችን በልዩ ንቅናቄ እና ትኩረት በመምራት የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ይሰራል፦ አቶ ማስረሻ በላቸዉ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት የግብርና ቢሮ የ2018 ዓ.ም የበልግና ተፋሰስ ልማት ሥራዎች ክልላዊ ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኋላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ከክልሉ አጠቃላይ ዓመታዊ ምርት 65 በመቶ ያህሉ በበልግ አዝመራ የሚመረት መሆኑን አስረድተዋል።

በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የግብርና ልማት ሥራዎችን በልዩ ንቅናቄና ትኩረት መምራት በመቻሉ በዘርፉ ውጤቶች እየተዘመገቡ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል አቶ ማስረሻ በላቸው።

በተጠናቀቀው በባለፈው የበልግ አዝመራ ከ394 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በዋና ዋና ሰብሎች በማልማት 14.6 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማግኘት መቻሉንም ጠቅሰዋል።

በክልሉ በተያዘው የበልግ አዝመራ በአጠቃላይ በሆልትካልቸርና በዋና ዋና ሰብሎች 4 መቶ 97 ሺ ሄክታር ማሳ በማልማት የምርት መጠን ዕድገትን ዘጠኝ በመቶ ለማሳደግ ይሰራል ነው ያሉት።

በዘንድሮ በልግ ወቅት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የግብዓት አጠቃቀም በተሟላ መልኩ በመጠቀም ምርታማነታችን አሁን ካለበት 37 ኩንታል በሄክታር ወደ 38 ከፍ ለማድረግ ዕቅድ መያዙንም ጠቁመዋል።

አክለውም አቶ ማስረሻ በላቸው በክልሉ የዘንድሮ በልግ ምርት ዘመን ሥራዎችን በልዩ ንቅናቄ እና ትኩረት በመምራት የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚሰራ በመሆኑ የሁሉም ርብርብ እንድጠናከርም አመላክቷል።

በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *