




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ በታርጫ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ዋና አፌጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ÷ ምክር ቤቱ ባለፊት የበጀት ዓመት ስድስት ወራት የአስፈጻሚ ተቋማት የተግባር አፈጻጸም በመገምገምና ክፍተቶችን በመለየት የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የበኩሉን ሚና መወጣቱን ገልጸዋል።
የታችኛው ምክር ቤቶችን በመደገፍ ጉባኤዎች በተያዘው ጊዜ እንዲከናወን ስሰራ መቆየቱን የገለጹት አፌጉባኤ ወንድሙ፥ በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል መታየቱን ጠቁመዋል።
በግማሽ ዓመቱ በምክር ቤቱ ተገምግሞ የተሻለ አፈጻጸም የታየባቸው የገቢ፣ የክልሉ ፖሊስ የማዕረግ ዕድገት፣ የመንግሥት ኪስ አፈጻጸም፣ የግብርና ዘርፍ ሥራዎች ላይ መሻሻል መታየቱን የገለጹት አፌጉባኤው፣
ይሁን እንጅ በክልሉ ሁሉም አከባቢ የገጠር መሬት አጠቃቀም አፈጻጸም በአዋጁ መሠረት ወጥነት ያለመኖር፣ የትራንስፖርት ቁጥጥር መላላት እንዲሁም ለትምህርት ቤቶ የብሎክ በጅት በተገቢው ያለመውረድ በጉድለት መገምገሙን ተናግረዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጭ ሠላማዊና ፍትሀዊ እንዲኾን የምክር ቤቱ አባላት የበኩላቸውን እንዲወጡ የጠየቁት አፌ-ጉባኤው ባለፋት አምስት ዓመታት የምክር ቤቱ አባላት የህዝብ አደራን ለመወጣት ላደረጉት የላቀ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
