
ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋለታ ነው። የወጪ ንግድ ገቢያችን ዋልታም ነው። በርካታ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሚሳተፍበት ነው።
ይህም ትልቅ ስፍራ እንዲሰጠው ያደርጋል። ግብርና ቢዝህ ዓመት 6 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት እንዲያመጣ ነው የታቀደው። የግብርናው ዘርፍ ከሌሎች ዘርፎች ልዩ ትኩረት ያገኘው ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነት ማግኘት አለባት፤ አምርታ መብላት ያልቻለች ሀገር ብሔራዊ ጥቀሞቿን ለማረጋገጥ ትቸገራለች በሚል የምግብ ሉዓላዊነትነ ለማረጋገጥ ግብ ይዘን ሰርትናል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት 27 ሚሊዮን በሴፍቲኔት የተያዙ ዜጎች ነበሩ፤ እነዚህን ከሴፍቲኔት ለማሸጋገር ሲሰራ ቆይቷል፤ በዚህም ለረጅክም ዘመናት በሴፍቲኔት ሲተዳደሩ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ወደ መተዳደር ተሸጋግረዋል። 23 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት ነጻ ወጥተዋል። ይህ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ማሳያ ስለሆነ ኩራት ሊሰማን ይገባል። ቀሪው ከ4 ሚሊዮን ያላነሰ ተረጂም ነጻ በማውጣት ኢትዮጵየን ሙሉ ለሙሉ የምግብ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች ሀገር ማድረግ አለብን። ለዚህም ሰፊ የሚታረስ መሬት አለን።
