
የዘንድሮው ዓመት በኢትዮጵያ ታሪክ በሁሉም ዘርፍ ታይቶ የማይታወቅ ድል የተመዘገበበት ነው፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በመጀመራችን ትርጉም ያለው ሚና፤ ትርጉም ያለው ውጤት ተገኝቶበታል፡፡
ወደ ማክሮ ኢኮኖሚ ያስገቡን ጉዳዮች አንዱ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶች ናቸው፤ በስራ አጥነት፣ በዋጋ ግሽበት፣ በወጪና ገቢ ንግድ ሚዛን መጓደል ሊገለፅ የሚችል ነው። ሁለተኛው ለግሉ ዘርፍ የስራ አካባቢው ምቹ አልነበረም። ሶስተኛው ምርታማነት ነው።
በግብርናም በኢንዱስትሪም ምርታማነታችን ውስን ነበር። ይህም በርካታ ተግዳሮቶች እነዲስተናገዱ አድርጓል። አራተኛው ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ሁኔታን አልፈጠርንም። እነዚህን ጉዳዮች ጨክነን በመፍታት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቱን መፍታት እንችላለን ብለን ነው ወደ ተግባር የገባነው።
የነበረውን ሳናፈርስ በነበረው ላይ የጎደለውን እየሞላን እና እያዘመንን የተሻለች፤ ታሪኳን ያልዘነጋች ኢትዮጵያን መስራት ይቻላል፡፡
እንደ እኛ ያለ የሌሎች እጅ እና ዕርዳታ እየጠበቀ ለሚኖር ሀገር ከፍተኛ ፈተና እንዳያጋጥመው ሆኗል፡፡
ኢትዮጵያ ሰፊ ፈተና ቢኖርባትም በመላው ሕዝብ ትብብር ባለፈው ዓመት በመላው የኢትዮጵያ የ8 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ማምጣት ተችሏል፡፡
