አመራሩ የንቅናቄው አጀንዳዎች ፋይዳን በመገንዘብ በላቀ ዝግጁነት መፈጸም ይገባል። አቶ ፍቅሬ አማን

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት እየተከናወኑ ያሉ የንቅናቄ አጀንዳዎች አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ውይይት በአመያ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን፥ በየደረጃው ያለው አመራር የንቅናቄው አጀንዳዎች ፋይዳን በተገቢው በመገንዘብ በላቀ ዝግጁነት መፈጸም እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።

ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውና ሀገራዊ ፋይዳቸው የላቁ አጀንዳዎች በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ መሪነት እየተተገበረ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ፍቅሬ የተግባር አፈጻጸም ከመዋቅር መዋቅር ልዩነት ያለ በመሆኑ የገጠሙ ችግሮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የጋራ ግንዛቤ መፈጠር ይገባል ብለዋል።

የክህሎት መሪ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ አንዱ በኾነውና በለውጡ መንግሥት ልዩ ትኩረት በተሰጠው የውጪ ሀገራት የሥራ ስምሪት አፈጻጸም በክልሉ አነስተኛ መሆኑን የገለጹት የጽ/ቤቱ ኃላፊ የተሰጠውን ኮታ በተገቢው ከመጠቀም አኳያ ማነቆ የኾኑ የአመለካከትና የተግባር ውስንነት ፈጥኖ በማረም በቀሪ አጭር ጊዜ አፈጻጸሙን ማሻሻል እንደሚገባ ተናግረዋል።

ተረጂነትንና ጠባቂነትን ትቶ የብልፅግናን ጉዞ የሚያረጋግጥ ትውልድ በመፍጠር

ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ለተጀመረው ተግባር የአፈጻጸም ችግር የኾኑ የመሬት አቅርቦት ፈጥኖ በማረም ወደ ምርት መገባት እንዳለበት ያስገነዘቡት አቶ ፍቅሬ በተግባሩ ላይ ወጥ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ካለው ሀገራዊ ፋይዳ መነሻ ተግባሩ በልዩ ትኩረት መምራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የኑሮ ውድነት ለማቃለል በተላይ በተከሞች የተጀመሩ የሰንበት ገበያ በማስፋት ውጤታማነቱን በየጊዜው እየገመገሙ ማጠናከር እንደሚገባ የገለጹት አቶ ፍቅሬ በጤናው ዘርፍ፥ በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ ወረርሽኝ ከመከላከል አኳያ አየተሰራ ያለው ተግባር መጠናከር አለበት ብለዋል።

ሌላኛው በፓርቲው ልዩ ትኩረት የተሰጠው የፋይዳ መታወቂያ መሆኑን ያብራሩት የጽ/ቤቱ ኃላፊ በየደረጃው ያለው አመራር የፋይዳ መታወቂያ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታውን ተገንዝበው ተግባሩን በመደገፍ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ መትጋት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የክልሉ ረዳት የመንግሥት ተጠሪዎች እና ሌሎች የባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የብልጽግና ፓርቲ መሪነት እየተተገበሩ ያሉ የንቅናቄ አጀንዳዎች አፈጻጸም ሪፖርት ከባለድርሻ ተቋማት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *