


በሶስት ቀናት ግምገማ መድረኩ የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ውጤታማነትን በጥልቀት መገምገም ተችሏል።
በመድረኩ የጠንካራ ፓርቲ፣ ጠንካራ መንግስት እንዲሁም ጠንካራ ሀገር የመገንባት ግቦችን መሰረት በማድረግ ባለፉት 6 ወራት ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸው የተጠቆመ ሲሆን ቀጣይነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባም መግባባት ላይ ተደርሷል።
ባለፉት ወራት የፖለቲካ፣ የአደረጃጀት እና የሕዝብ ንቅናቄ ስራዎች አፈጻጸም በጥልቀት በመገምገም ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባም ተጠቁሟል።
ስኬቶችን ለማስቀጠል፣ ክፍቶችን ለመሙላት እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ተጠቁሟል።
በግምገማው በፓርቲያችን መዋቅር ግንባር ቀደም ተሣትፎ የሚከናወኑ የንቅናቄ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
በዚህም የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ፣ ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ እንዲሁም ከተረጂነት መላቀቅ ሀገራዊ ግብን ለማሳካት የተሰሩ ውጤታማነት ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።
