
በዞኑ አዲዮ ወረዳግራዋ ሽሽማ ቀበሌ በሌ ልማት ቡድን ተብሎ በሚጠራበት ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት በጣለዉ ከባድ ዝናብ ባስከተለዉ የመሬት መንሸራተት አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት በመኖሪያ ቤት ዉስጥ እንዳሉ ህይወታቸዉ ማለፋን ፖሊስ ገልጿል።
በአደጋዉ ሁለት መኖሪያ ቤቶች በናዳዉ መወሰዱን ያመለከተዉ ፖሊስ በአከባቢዉ የሚጥለዉ ከባድ ዝናብ የነፍስ አድኑን ስራ አስቸጋሪ አድርጎታል።
