






ይህ የተባለው በሸካ ዞን ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በትኩረት በሚፈፀሙ ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት በቴፒ ከተማ እየተካሄደ በሚገኝበት ወቅት ነው።
የውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በወቅቱ እንደተናገሩት የዞኑን ልማትና እድገት ለማፋጠን እንዲሁም የዞኑን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ርብርብ ወሳኝ ነው ብለዋል።
አቶ አበበ አክለውም ለዞኑ ልማትና እድገት እንዲሁም ለህብረተሰቡ ኑሮ መሻሻል የአመራሩ በተግባርና በአስተሳሰብ አንድ መሆን ሚናው የጎላ ነው ሲሉም ጠቁመዋል።
በዞኑ ሠላምን ለማረጋገጥ የተሠራው ስራ በልማትም ሊደገም እንደሚገባ ገልፀው አሁንም ቢሆን የሠላምና ፀጥታ ስራ ከትኩረት ማዕከላችን አንዱ ነው ብለዋል አቶ አበበ።
በዋና ዋና የንቅናቄ አጀንዳዎች የተሻለ ዉጤት ለማምጣት ጠንክሮ፣ተግባብቶና ተናቦ መስራት ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ በአፅንኦት አንስተዋል።
በዞኑ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በሚከናወኑ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ዕቅድ በአካባቢው ተወላጅ ምሁራንና አመራሮች እየቀረበ ይገኛል።
ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ፣ በከተማ ልማት እንዲሁም በፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፎች በልዩ ትኩረት በሚፈፀሙ ተግባራት ዙሪያ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን ሰፊ ውይይት እንደሚደረግም ተጠቁሟል።
ከተማ ልማት፣ግብርና፣ገቢ አሰባሰብ፣ትምህርትና ጤና ዘርፍ ላይ እመርታ ማስመዝገብ ከርብርብ ማዕከላት ዋነኞቹ እንደሆኑም ተገልጿል።
በመድረኩ የዞን ፣የሁሉም ወረዳና ከተማ አጠቃላይ አመራሮች እንዲሁም በተለያዩ አካባቢ የሚገኙ የዞኑ ተወላጅ ምሁራን እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን ውይይቱ ለ2 ተከታታይ ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል።
