በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር ይሸፈናል

Spread the love

በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር እንደሚሸፈን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ ወቅታዊ የግብርና መረጃዎችን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ በመኸር እርሻው 20 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት በአነስተኛ ይዞታ ባላቸው አርሶ አደሮች መልማቱን አስታውሰው፤ በሰፋፊ እርሻም ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥም እስካሁን 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር ላይ ምርት መሰብሰቡን ተናግረዋል።

በአሁኑ ጊዜ ምርት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሰብል ስብሰባ መጀመሩን ጠቁመው፤ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ምርቱን እንዳያበላሽ በርብርብ መሰብሰብ እንዳለበት ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በዘንድሮ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን መታቀዱን ጠቁመዋል።

እስካሁን በበጋ የመስኖ ሥራ 850 ሺህ ሄክታር የመሬት ዝግጅት መደረጉን ጠቁመው፤ 505 ሺህ ሄክታር የሚሆነው በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል።

ለ2017/18 የምርት ዘመን የሚውል የ24 ሚሊየን ኩንታል የማዳበሪያ ግዥ ሂደት መጀመሩን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ለኢትዮጵያ አፈር ተስማሚ የሆኑ ማዳበሪያ ለማቅረብ ሂደቶች ተጀምረዋል ብለዋል።

በዘንድሮው ዓመት 2 ሚሊየን ኩንታል ምርጥ ዘር ለማቅረብ መታቀዱንም አመልክተዋል።

ከሌማት ትሩፋት አኳያም ዘንድሮ 150 ሚሊየን ጫጩቶችን ለማሠራጨት ዕቅድ ተይዞ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንም እንዲሁ።

12 ቢሊየን ሊትር የወተት ምርት ለማግኘት መታቀዱንም አንስተዋል።

በዓመቱ 8 ቢሊየን የዶሮ እንቁላል፣ 218 ሺህ ቶን ሥጋ እንዲሁም 297 ሺህ ቶን የማር ምርት ለማምረት የሚያስችል አቅም መፈጠሩንም ጠቁመዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *