የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ውይይት እየተካሄደ ነው

Spread the love

በመድረኩ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪውን መዋቅራዊ ችግሮች በቅንጅት ከመፍታት እና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የንቅናቄውን አፈፃፀም ለመገምገም እና ለመደገፍ የሚኒስትሮች የክትትል እና የድጋፍ ቡድን በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በቅርቡ የመስክ ምልከታ በማድረግ ድጋፍ ማድረጉም ተመላክቷል፡፡

ቡድኑ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አፈፃፀምን በተመለከተ ባመጣው ግኝት ላይና አፈፃፀሙ በየክልሎች ያለበትን ደረጃ ከስቲሪንግ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት በማድረግ በቀጣይ ቀሪ ግማሽ ዓመት የዘርፉን እቅድ ለማሳካት የሚያግዝ የስራ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ተጠቁሟል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *