




በካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በአቶ እንዳሻው ከበደና በዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በአቶ አጥናፉ ሀይሌ የተመራ የዞን ከፍተኛ አመራሮች ቡድን በዳካ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል።
ለአረጋውያን የተሰራውን መኖሪያ ቤት መርቀው ያስረከቡ ሲሆን ፤ ለአዳዲስ ግንባታዎች የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ፤ መንግስት ዜጋ-ተኮር ስራዎችን በሁሉም ቦታ በማስፋፋት አቅመ-ደካሞችን ለመርዳት እየሰራ ነው ብለዋል።
የአረጋውያን ቤት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ከተማ አስተዳደሩና ህብረተሰቡ ላደረጉት ትብብር አመስግነዋል።
የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠላቸው የልማት ስራዎች መካከል የዳካ ሞዴል ቅድመ-አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ እና የዳካ ጤና ጣቢያ ማስፋፊያና ደረጃ ማሳደጊያ ግንባታ ይገኙበታል።
ለጤና ጣቢያ ማስፋፊያና ደረጃ ማሳደጊያ ግንባታ የዞኑ አስተዳደር 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ተናግረዋል።
ግንባታው በፍጥነት ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል ያለው ቦንጋ ኤፍኤም 97.4 ነው።
