በኮንታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት “የአስተሳሰብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በዞን ማዕከል ዞናዊ የአመራር አቅም ግንባታ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

Spread the love

በመድረኩ ሀገራዊ፣ ክልላዊና ዞናዊ ነባራዊ ሁኔታ የሚዳስስ ሰነድ ቀርቦ በ2 ቡድን ውይይት የሚደረግ ሲሆን አመራሩ ለቀጣይ ተልዕኮዎች ራሱን እንዲያዘጋጅ ለማስቻል ያለመ ስለመሆኑ ተመላክቷል።

በመድረኩ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙን ጨምሮ የዞን አመራሮች፣ የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ስራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *