ዞናዊ ነበራዊ ሁኔታን መሠረት ያደረገ አጠቃላይ የዞን አመራርና ወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

Spread the love

የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዞናዊ ነባራዊ ሁኔታን መሠረት ያደረገ አጠቃላይ የዞን አመራርና የወረዳ እና ከተማ አስዳደር አስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ፥ የመድረኩ ዓላማ ቀደም ሲል በተሰጡ የአመራር መድረኮች የተገኙ አቅሞችን በማቀናጀትና በአመራር መካከል የተግባር አንድነትን በመፍጠር የህዝብ የልማት አቅሞችን በማቀናጀት ወደ ተግባር እንድገባ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል ።

በዞኑ ውስጥ ያሉ ፀጋዎችን በተገቢው በመለየት በተቀናጀ መልኩ ወደ ልማት በመግባት የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ፈጥኖ ከመፍታት አኳያ አመራሩ ከወትሮ በተለየ መልኩ ወደ ተግባር እንድገባ የሚያስችል መድረክ መሆኑን አቶ እንዳሻው ተናግሯል ሲል የዘገበው የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *