




በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የክልሉ ብዝሃ ማዕከል አንዱ በሆነው በታርጫ ከተማ የተገነባው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (የኢቢሲ) ስቱዲዮ በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምረዋል።
የኢቢስ ወደ ይዘት የጉዞ አካል የሆነው አዲሱ የኢቢሲ ታርጫ ስቱዲዮን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እና የኢቢስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሴ ተገኝተው መርቀዋል ።
የተመረቀው የኢቢሲ አዲሱ ስቱዲዮ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ በመሆን የክልሉን እና የአካባቢውን እምቅ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብቶችን አጉልቶ ለማሳየት፣ የክልሉን ገጽታ ለመገንባት፣ ለህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር ብሎም በሁሉም ዘርፍ የመረጃ ተደራሺነትን በማስፋት የህዝብ ድምፅ ለመሆን አይነተኛ ሚና እንዳለው ተመልክቷል ።
የምረቃ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የፌደራል፣ የክልል፣ የዳውሮ ዞንና የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ከተለያየ አካባቢዎች የተውጣጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል ።
በጌታሁን ግርማ
