

የንግድ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የተደገፈና የተደራጀ የማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።
ዛሬ የአገር ውስጥ ንግድን የተመለከተ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)፣ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት፣ ምሁራን፣ የሸማች ማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል።
የንግድ ስርዓቱ ከብልሹ አሰራሮች የፀዳና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ገልጸዋል።
ውይይቱ በአገር ውስጥ ንግድ የተገኙ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በዘርፋ ያለው አንድምታ ላይ ያተኮረ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
