ሀገር አቀፍ የወጣቶች የሰላምና ደህንነት ኮንፍረንስ እየተካሄደ ይገኛል

Spread the love

ኮንፈረንሱ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ልማት ፈንድ ጋር በመተባበር “ወጣት የሰላም ባለቤት” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ፣ በተባበሩት መንግስታት የስነ ህዝብ ልማት ፈንድ ተወካይ ኮፊ ኮዮሜ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ወጣቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

መድረኩ ወጣቶች ለሀገር ግንባታ ያላቸው ሚና እና ሰላምን ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ ለመመካከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *