


የሚዛን አማን ከተማን ዕድገትና የህዝቡን ፍላጎት ባማከለ መልኩ መልሶ ለማልማት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።
የኮሪደር ልማት ሥራን በከተማ አስተዳደር ደረጃ ማስጀመር እና ጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን ማስጀመርን ዓለማ ያደረገ ግንዛቤ ማስጨበጫና ምክክር ነው እየተካሄደ ያለው።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን ከተሞች ቀደም ሲል ደረጃውን ባልጠበቀ ፕላን የተመሠረቱ ሲሆን አሁን ላይ ያለውን ዕድገትና ፍላጎት ያማከለ አድርጎ መልሶ ማልማት ከዚህ ትውልድ ይጠበቃል ብለዋል።
የሚዛን አማን ከተማን አሁን ላይ ያለውን ዕድገትና ፍላጎት ያማከለ አድርጎ መልሶ ለማልማት ከከተማው ነዋሪዎችና አመራሩን ጨምሮ ከመንግስት ባለድርሻ አካላት በሀላፊነትና በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
ሚዛን አማን በፈጣን ዕድገት ውስጥ የምትገኝና ብዙ ተስፋና ጸጋ ያላት ከተማ በመሆኗ ከተማዋን ለኑሮ ምቹ ፣ ውብ ፣ ጽዱና ማራኪ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የማድረግ ጉዳይ የዚህ ትውልድ ውዴታ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነው ብለዋል።
የሚዛን አማን አተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም በበኩላቸው ኢትዮጵያ ጽዱ የምትሆነው በሁሉም አካባቢ ጽዳት ሲጠበቅ ነውና በኮሪደር ልማት የመንገድ ጥበትን ለመቅረፍ አማራጭ መንገድን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።
ተግባሩን ሁሉን ያሳተፈ በማድረግ ሚዛንን ደረጃዋን ማሳደግ በትኩረት ይሰራል ከንቲባዉ ማለታቸዉን የዘገበዉ ሚዛን ፋና ኤፍ ነዉ።
ህዝቡም ከመንግስት ጎን በመሆን የከተማዋን ዕድገት ሊያፋጥንና ሊተባበር ይገባል ብለዋል።
