መከላከያ ሠራዊቱ ህገ መንግስታዊ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ::

Spread the love

መከላከያ ሠራዊቱ ህገ መንግስታዊ ተልዕኮውን በብቃት የመወጣት አኩሪ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ አስታወቁ።

ብላቴ የሚገኘው የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን 42ኛ ዙር የኢትዮጵያ ኮርስ መሰረታዊ ኮማንዶ ዛሬ አስመርቋል።

በዚህ ወቅት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ባደረጉት ንግግር፤ መከላከያ ሠራዊት የሀገሪቱን ህዝቦች ሰላምና ሉዓላዊነት የማስከበር ተልዕኮውን እየተወጣ በላቀ ብቃት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

መከላከያ ሠራዊቱ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ፤ ይህም የሠራዊቱ ዋነኛ እሴት መሆኑን ተናግረዋል።

መከላከያ ሠራዊቱ ህገ መንግስታዊ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ እንደመጣ ሁሉ ወደ ፊትም ይህንን አኩሪ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የዛሬ ተመራቂዎች በገቡት ቃል መሰረት ሀገራቸውን በማስቀደም የሚሳጣቸውን ግዳጅ በብቃት እንዲወጡም አሳስበዋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የኢፌዴሪ ጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ፣ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሹማ አብደታ፣ ሌሎች ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ተገኝተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *