

ኢትዮጵያ በርካታ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ የቱሪስት መስህቦች ያሏት አገር ነች፡፡ ያሏትን የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ታሪካዊ ቅርሶች እንዲሁም የማይዳሰሱ ትውፊቶች በአግባቡ ለመጠቀም ፖሊሲዎችን እንደ አዲስ በመከለስ በዘርፉ ለውጥ ለማምጣት እየታተረች ትገኛለች፡፡
እነዚህን በርካታ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች በአግባቡ በማልማት ከዘርፉ የሚፈለገውን ያህል ኢኮኖሚዊ ጥቅም ማግኘት እንደሚያስፈልግ ይታመናል፡፡ በተለይ ቱሪዝም ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው ዘርፍ መሆኑ በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡
የቱሪዝም ዘርፉ ከማኅበራዊ ፋይዳው ይልቅ ወደ ኢኮኖሚዊ ዕድገት ሽግግር ያደገበት ሁኔታ በመፈጠሩን ይህንንም ዘርፍ በአግባቡ መጠቀምና በመንከባከብ የተሻለ ዕድገት ማስመዝገብ ያስፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ ለቱሪዝም ምቹ ከሆኑና በተፈጥሮ ሀብታቸው ከሚጠቀሱ አካባቢዎች መካከል ደግሞ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አንዱ ነው።
በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ክልሉን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በተሰሩ ሥራዎች ውጤት እየተመዘገበ መጥቷል።
ክልሉ ለቱሪዝም ምቹ የሆኑና የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስቡ በርካታ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊ እና ባህላዊ ሀብቶች መገኛ ስፍራ ቢሆንም ባለፉት ጊዜያት ትኩረት ሳይሰጣቸው ቆይቷል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እንደሀገር በቱሪዝም ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም አልምቶ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግና ዘርፉን ለማነቃቃት በመንግስት የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው።
የቱሪዝም መዳረሻዎች በተገቢው በመለየት እና በመልማት ቱሪዝም ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግና ያሉትን ችግሮች ለመፍታት በልዩ ትኩረት እየሠራ መሆኑን የካፋ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታውቋል፡፡
የካፋ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ነፃነት ብርሃኑ በዞኑ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን ላይቶ በመልማት ለጎብኝዎች ክፍት ከማድረግ አኳያ ዘርፈብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
የወረዳ መዋቅሮች የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት ለጎብኚዎች ክፍት ለማድረግ እያከናወኑት ያለው ተግባር ትልቅ ሚና አለው።
በዞኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዞኑ ዋና አስተዳደር መልካም ፍቃድ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኝና ከነዚህም መካከል የመንገድ መሠረተ ልማት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ ነጻነት እንዳሉት በዞኑ ለቱሪዝም ምቹ የሆኑ ፏፏቴዎች፣ የተፈጥሮ ድልድይ፣ ዋሻዎች፣ የተለያዩ አዕዋፋት እንዲሁም ታሪካዊና ጥንታዊ የእምነት ቦታዎች ይገኛሉ ብለዋል።
በካፋ ዞን ከ 40 በላይ የተለዩ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 9ኙ በሀር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ጎብኝዎች እየተጎበኘ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡
ከነዚህም ውስጥ በዋናነት ዳዲቤን ፊል ውሃ ፣ ማንክራ እናት ቡና፣ ጉርጉቶ የእግዝዬር ድልድይ፣ ኩቲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንና በሃ ቅዱስ ጊዮርግስ ቤተክርስቲያን እና የበርታ ፏፏቴ የተለያዩ ተመራማርዎች ያረጋገጡት ስፍራዎች መሆናቸውንአቶ ነጻነት ጠቅሰዋል ፡፡
ታርካዊ የእምነት ቦታዎች በካፋ ዞን ከ500 ዓመት በፊት ጀምሮ በተለያዩ ውቅት ተመስርቶ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በ1529 ዓም የተመሰረተው የኩቲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንና በሃ ቅዱስ ጊዮርግስ ቤተክርስቲያን መሆናቸውን ጠቅሰው በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተመሰረተው የቶንጎላ መስጊድም እንደሚገኝ አቶ ነፃነት ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ በዞኑ በዋናነት 3 የቱርስት መዳረሻነት የተያዙና የተለዩ ቦታዎች እንዲለሙ የታቀደው እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል ፡፡
የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች፤ ዳዲቤን ፊል ውሃ፣ ጉርጉቶ የእግዝዬር ድልድይና የበርታ ፏፏቴ አካባቢዎችን በመንገድ መሠረተ ልማት ለማስተሳሰር ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ነፃነት አመልክተዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በዞኑ ቅርሶች ይዘታቸው ሳይለወጥ ለትውልድ እንዲተላለፉና የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆኑ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ጥገና እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
የቱሪዝም ዘርፉን ከመሠረተ ልማት፣ ከአካባቢ ጥበቃ እንዲሁም ከብዝኃ ሕይወት ጥበቃን በማካታት መሥራት አንደሚያስፈልግ አስታውሰው በዚህም ረገድ ሁለም ትብብርሩን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።


የዞኑ መንግስት ለዘመናት ህዝቡ ጠብቆ ያቆየውን የቱሪዝም ሀብት ከተለያዩ አደጋዎች ለመታደግ በትኩረት ይሰራል ሲሉም አንስተዋል።
