በአሁኑ ወቅት አለማችን ክፉኛ እያሳሰቧት ከሚገኙ ጉዳይ ሠው ሠራሽና የተፈጥሮ በሽታዎች ውስጥ የመንገድ ትራፊክ አደጋ አንዱ ሆኖ ይገኛል።

Spread the love

ትንሽ ጥንቃቄ በማድረግ በቀላሉ ሊከለከሉት በሚችሉት በዚህ አደጋየብዙዎች ደጃፍ እየተዘጋ፣ቤተሰብ እየተበተነ፣ለአካል ጉዳት እየተዳረገ ንብረቶች እየወደሙና ሀገራትም ከድህነት ለመላቀቅ የሚያደርጉትን ጥረት እየተጓተተ ነው።

እንደዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት መሠረት አደጋው ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች በጣም የከፋ ከመሆኑም በላይ እነዚህ ሀገሮች ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ሀገሮች ከሚደርስባቸው የሞት አደጋ እጥፍ የሚደርስባቸው ሲሆን በዓለም ከሚደርሰው የሞት አደጋ 90% በእነዚህ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች የሚደርስ መሆኑን መረጃው ያሳያል።

ለሀገራችን ኢትዮጵያ የገቢና የወጪ እቃዎች ዝውውር 90% እንዲሁም ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ክንውኖች ከሚደርሰው የመንገደኞች እንቅስቃሴ 95% ያህሉ አገልግሎት የሚያገኘው በመንገድ ትራንስፖርት አማካኝነት ነው።

በመሆኑም ይህ ዘርፍ ለሀገር ልማትና ዕድገት የጀርባ አጥንት በመሆን እያበረከተ ካለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ አንጻር ዘርፉ በተገቢው፣ በተጠናከረ እንዲሁም በተቀናጀ መመራት ይፈልጋል ።

በክልላችንም የትራፊክ አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ከፍተኛ አደጋ እያደረሰ ይገኛል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ በሰው ህይወት፣አካልና ንብረት ላይ የሚያደርሰው አደጋ ከግንዛቤ በማስገባት አደጋዎችን ሊያስከትሉ የሚችሉ መንሰኤዎችን በመለየት የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን በማጠናከር የአደጋዎችን መጠን ለመቀነስ እየሰራ  ይገኛል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መረጃና ስታስትክስ ድቪዥን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ወንደወሰን ወንድሙ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 236 አደጋዎች ከተከሰተበት መካከል 51 የሞት 152 ከባድ የአካል ጉዳት፣ 25 ቀላል እና 8 ንብረት አደጋዎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በዚህም በተያዘው በ2016 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ብቻ 430 ህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ሞት፣ከባድ እና የቀላል አካል ጉዳት አደጋዎች መድረሳቸውን አብራርተዋል።

እንደ ምክትል ኢንስፔክተር ወንድወሰን ገለጻ በክልሉ በስድስቱም ዞኖች የትራፊክ አደጋዎች የሚከሰቱ ቢሆኑም በቤንች ሸኮና በካፋ ዞኖች በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋዎች ክስተት ይስተዋላል ብለዋል።

ለትራፍክ አደጋዎች ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር፣ቅድሚያ መከልከል፣የአሽከርካሪዎች ብቃት ማነስ፣የተሽከርካሪዎች ቴክኒክ ውስንነት፣ትርፍ መጫን እንዲሁም አልፎ አልፎ የአየር ሁኔታ መቀያየር እና ሌሎች ዋነኛ መንስኤዎች እንደሆናቸውም የትራፊክ አደጋ መረጃና ስታስትክስ ድቪዥን ኃላፊ ተናግረዋል።

የአደጋውን አስከፊነትና አሳሳቢነት አንፃር በታችኛው ባሉት መዋቅሮች በትምህርት ቤቶች፣በኃይማኖት ተቋማትና ህብረተሰቡ በሚበዙባቸው ቦታዎች የሚፈጠሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ቢኖሩም በቂ የሚባል ስላይደለ በቀጣይ በክልሉ ባሉት ስድስቱም ዞኖች ላይ የአደጋዉን መጠን ለመቀነስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።

በዚህም የአሽከርካሪዎች ተሃድሶ ስልጠና መስጠት፣ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮችና የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት የንቅናቄ መድረኮችን መፍጠር፣ፍጥነት መቀነሻዎችን መገደብና ለእግረኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን ለመስጠት አቅጣጫዎች ተቀምጧል ነው ያሉት ።

ህብረተሰቡም መንገድ ሲያቋርጥ ለእግረኛ የተፈቀደ መንገድ ብቻ በመጠቀም ራሱን ከአደጋ እንዲጠበቅና አሽከርካሪዎችም ሙያዊ ኃላፊነት በተሞላበት ማሽከርከር እንደሚጠበቅባቸውም ምክትል ኢንስፔክተር ወንደወሰን ወንድሙ አስገንዝበዋል።

አክለውም ምክትል ኢንስፔክተሩ የክልሉ አቅም መድረስ በሚችልባቸው ልክ የክትትልና ቁጥጥር ተግባራት የሚጠናከር ሲሆን ያለህብተሰብ የትራፊክ አደጋውን መቀነስም ሆነ መግታት የማይቻል በመሆኑ ሁሉም በትብብር እንዲሰራ ጠይቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *