





የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የግብርና ቢሮ እና የኮንታ ዞን አመራሮች በኮንታ ኮይሻ ወረዳ የበልግ አዝመራ የተሰሩ የእርሻ ስራዎችን ጉብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም በበልግ የለማዉ በቆሎ፣ ሰሊጥና ካሳባ ምርት እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራ አካል የሆነውን ሙዝ ያለበትን ደረጃ ጎበኝተዋል።
በጉብኝት ወቅት የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታመነ በቀለ በወረዳ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ የግብርና ስራዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው ስሉ ተናግረዋል።
በወረዳው እየለማ ያለው የሰሊጥ ምርት ለሌሎች አከባቢዎች ተሞክሮ የሚሆን ነው ስሉ ተናግረው በግብርና ዘርፍ ላይ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
በተጨማሪም ወረዳው በግብርና ዘርፍ ውጤታማ የመሆን ሙሉ አቅም እንዳለውና አቅሙንም ለመጠቀም እያደረገ ያለው ርብርብ የሚበረታታ ነዉ ብለዉ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ክልሉ ልዩ ድጋፍ ያደርጋል ስሉም ተናግረዋል።
በወረዳው የበልግ ተግባራት አፈጻጸም አመርቂ ነው ያሉት የኮንታ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስረቀ መምሪያ ኃላፊ አቶ ማስረሻ አደሮ እንደ ወረዳ በበልግ ተግባር ከታቀደው 90% አዝርዕት ሰብል መሆኑን ገልጸው በአሁኑ ሰዓት ከእቅዱ በላይ ማሳዎች በአዝርዕት ሰብል መሸፈናቸውን አንስተዋል።
ወረዳው በራሱ ተነሳሽነት ከ320 ሄ/ር በላይ እያለማ ያለው የሰሊጥ ምርት በእጅጉ የሚደገፍ ነው ያሉት ዋና መምሪያ ኃላፊው ከሰብል ጥበቃ አንጻር የማሳ አረም ቁጥጥርና የተባይ አሰሳ ከዞንም አልፎ ለክልሉ ትልቅ ተሞክሮ መሆን የሚችል ነው ስሉ ተናግረዋል።
እንደ ወረዳ በበልግ ከታቀው አዝርዕት ሰብሎች መካከል የቅባት ዕህል የሆነው ሰሊጥ በዋናነት የሚጠቀስ ስሆን በክላስተር 322.625 ሄ/ር በላይ መሬት መሸፈኑን የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ጎበዜ ሲል የዘገበዉ የኮንታ ኮይሻ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።
