

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኒኮዚ አዌላ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም፥ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን እየተደረገ ባለው ጥረት ላይ መክረዋል።
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል መሆኗ ለዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የጎላ ሚና እንዳለውም ተጠቁሟል።
በመሆኑም በፈረንጆቹ መጋቢት 2026 በካሜሩን ያውንዴ በሚካሄደው 14ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ጉባዔ የኢትዮጵያን አባልነት ለማረጋገጥ፤ቀሪ ሥራዎች እንዲፋጠኑ በሁለቱም ወገን በኩል ቁርጠኝነት መኖሩ ተገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
