






የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ደን፣አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ አመራሮችና የሬድ ፕላስ ፕሮግራም አስተባባሪዎችና ሠራተኞች ችግኝ ተከሉ።
ቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ቃሻ ቀበሌ በሬድ ፕላስ ፕሮግራም የተዘጋጁ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን በተዘጋጀው 2 ሺህ ጉድጓድ ላይ ተከለ ተከናውኗል ።
በዚሁ ወቅት የክልሉ ደን፣አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢ/ር አስራት ገ/ማሪያም የአረንጓዴ አሻራ መረሐ ግብር መፈጸም ለቢሮው አማራጭ የለለው ተግባር እንደሆነም ተናግረዋል።
በክልሉ በተፈጥሮ ሀብት ከሚሰሩ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች መካከል የሬድ ፕላስ ፕሮግራም ትልቁን ድርሻ ወስዶ እየተቀሳቀሰ ነው ያሉት ዶ/ር ኢ/ሩ የተራቆቱ አከባቢዎችን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ባላቸው ችግኞች ለመሸፈን ትኩረት ይደረጋል ብለዋል።
ሀብትን ማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን ኑሮን በደኑ ያደረጉና ደኑን ጠብቆ ያቆዩ ማህበረሰብ በካርበን ልቀት ክፊያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሰራልም ብለዋል።
የክልሉ የሬድ ፕላስ ፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር የርቾ ብርሃኑ በክልሉ የ’ሬድ ፕላስ ፕሮግራም በዘንድሮ ዓመት ከ10 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ግብ ጥሎ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል።
ከሚተከሉት ችግኞች ከመቶ 70% የሚሆኑ ሀገር በቀል፣ለምግብነት የሚውሉ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ መከላከልና ለስነምህዳር ጥበቃ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ያላቸውና 30% የውጭ ዝሪያ ያላቸው ችግኞች ናቸው ብለዋል አስተባባሪው።
ከተከላው ባሻገር በቃሻ አሳታፊ ደን አስተዳዳር ህብረት ስራ ማህበር በሬድ ፕላስ እንቨስትመንት ባለፉት ጊዜያት የተተከሉት ችግኞች ፅድቀት ያሉበት ደረጃና ለተከላ የተዘጋጁ ችግኞች ጉብኝትና ምርጥ ተሞክሮ ልምድ ልውውጥ ተደርጓል።
በዚህም በቀበሌው በአሳታፊ ደን አስተዳዳር ህብረት ስራ ማህበር በሬድ ፕላስ እንቨስትመንት እስካሁን 29 ሄክታር መሬት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የተፈጥሮ ደን ደርቻ ተከላ እንደተደረም የቤንች ሸኮ ዞን የሬድ ፕላስ አስተባባሪ አቶ ሁሰን ከድር ገለጻ አድርጓል።
በመረሃ ግብሩ የክልሉ ደን፣አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ አመራሮችና ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ የሬድ ፕላስ ፕሮግራም አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በፍቅር ከበደ
