የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል ምን እየተሰራ ነው?

Spread the love

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

“ከፍተኛ ትምህርት ለላቀ ተፅዕኖ” በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክርቤት ጉባዔ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል።

የትምህርት ሚኒስትር ድዔታ ኮራ ጡሽኔ በጉባዔው መክፈቻ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ የመምህራን ልማት፣ ግብዓት ማሟላት፣ የመማር ማስተማሩን ሂደት መከታተል እና ውጤቱን መለካት ላይ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።

አክለውም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጀመሩ የለውጥ ሂደቶችንና ተግባራት በውጤት መለካትና መገምገም መጀመሩን አቶ ኮራ ተናግረዋል ።

ጉባዔው የዓመቱን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ሂደት ለመገምገም እና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት የሚደረግበት መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ለመሆን እያደረጉት ያለው ዝግጅትና መስፈርቶችን ለማሟላት እያከናወኑ ያሉት የብቃት ዝግጅት በጉባዔው እንደሚገመገም አቶ ኩራ ተናግረዋል።

የጎንደር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) በበኩላቸው ጉባዔው ዩኒቨርሲቲው የምስረታ በዓሉን እያከበረ ባለበት ወቅት መከናወኑ ልዩ እንደሚያደርገው ገልጸው፤ ዩኒቨርስቲው ከተመሠረተ ጀምሮ በርካታ ለወጥ ያመጡ ሥራዎችን መስራቱን አስታውሰዋል።

ከእነዚህም መካከል የጎንደር የቃል ኪዳን ቤተሰብ አንዱ ሲሆን ይህም የመማር ማስማሩን ሰላማዊና ውጤታማ በማድረግ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን ነው ዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት የተናገሩት።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዓለም አቀፋዊ ባህሪ ያላቸው በመሆኑ በሀገሪቱ የሚገኙ የትምህር ተቋማት እርስ በእርስ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግም አክለው ገልፀዋል ።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ የሁሉም ዩኒቨርስቲዎች አመራሮች፣ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላትና የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ተገኝተዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *