




በቤንች ሸኮ ዞን የ3ኛ ዙር “የህልም ጉልበት፣ ለእምርታዊ ዕድገት!” በሚል መርህ ለተከታታይ 10 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ሀገራዊ ስልጠና ተጠናቀቀ።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን በስልጠናው ማጠቃለያ እንደተናገሩት በሰው ሀብት ላይ የተደረገው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ውጤታማነቱ የሚረጋገጠው አመራሩ ተመልሶ በሚያስመዘግበው የተግባር አፈፃፀም መሆኑን ተናግረዋል።
ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ጉዳዮችን ከአከባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በመተንተን ለመረዳትና የአስተሳሰብ አድማሳቸውን ለማስፋት የሚያስችል የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና በመውሰዳቸው በቀጣይ በተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
የፓርቲያችንን ጥልቅ እሳቤዎች በተግባር በመተርጎም የህዝባችን ህይወት በማሻሻል ሁለንተናዊ ብልፅግናችንን ለማረጋገጥ ተቋማትን በፅኑ መሰረት ላይ መገንባት ወሳኝ ነው ብለዋል።
በስልጠናው የተገኘውን እውቀትና ልምድ ወደ ውጤት በመቀየር አመራሩ የመሪነቱን ሚናውን በሚገባ በመወጣት ሀገራዊ ተልዕኮዎችን ማሳካት ይገባል ሲሉ አቶ ሀብታሙ ጠቁመዋል።
በዞኑ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ የተጀመሩ ሥራዎችን በስልጠናው የተገኘውን በመጠቀም በርካታ ሥራዎች እንደሚጠበቅ አቶ ሀብታሙ ጠቁመዋል።
በጤና ፣በትምህርት ፣በግብርና ፣በመሠረተ ልማት ፣ በሠላም እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ለውጥ በሚያመጣ መልኩ እየተመራ መሆኑን አቶ ሀብታሙ ገልፀው ለውጤታማነቱ አመራሩ ከህዝቡ ጋር በመተባበር በቀጣይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
እያንዳንዱ አመራር ወደ የሚመራው ተቋም ሲመለስ ምን ለማሳካት ነው የተቀመጥኩት የሚለውን የሚመልስ መሆን አለብት ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል ።
አቶ ሀብታሙ አክለውም አመራር ስነ -ምግባርን በመላበስ ፣ የሥራ ባህልን በማዳበር በሁሉም ዘርፍ የሚጠበቀውን ለውጥ ለማምጣት አስተዋጽኦው ከፍተኛ በመሆኑ ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደግፌ ኩድን በበኩላቸው በአመራሩ መካከል የታዩ የተግባር አፈፃፀም ልዩነቶችን የሚያጠብ መሆኑን ተናግረዋል ።
አመራሩ በስልጠናው የወሰደውን ተሞክሮ ወደ ተግባር በመቀየር የህዝብ አገልጋይነት እና ተጠቃማነት ላይ መታየት አለበት ሲሉ አቶ ደግፌ ጠቁመዋል።
እየታዩ ያሉ የለውጥ ስኬቶች ላይ ያለውን የግንዛቤ ክፍተት በመሙላት ተመሳሳይ ግንዛቤ የተያዘበት መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ተናግረዋል ።
በስልጠናው ከተሳተፉት መካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት በስልጠናው ሀገር የሚያሻግሩ ፣አቅምን የሚያጎለብቱ መሆኑን ጠቁመው አመራሩ ስነ ምግባርን በመላበስ ከማገልገል አንፃር የሚጠበቅብንን ለመወጣት ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል።
