መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የጀመረው ስራ ዳር እንድደርስ የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።

Spread the love

በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሸካ ግሪን ላንድና ማሻ ጃንግል ቡናና ቅመማቅመም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያስገነቡት ትምህርት ቤት ተመረቀ።

በማሻ ወረዳ የሻ አካኮ ቀበሌ 8.4 ሚሊዮን ብር ወጪ የሸካ ግሪን ላንድና ማሻ ጃንግል ቡናና ቅመማቅመም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤቶች በአቶ ግደይ በርሄና አቶ መብራቴ ኪዳኔና ከእኔ ቤተሰቦቻቸው ያስገነቡት 8 ክፍል ያለው ህንጻ ነው ዛሬ የተመረቀው።

በህንጻ ምረቃው ላይ የተገኙት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ እንደተናገሩት እንደዞን በግብርና ዘርፍ 46 ባለሀብቶች የተሰማሩት ሲሆን ከነዚህም መካከል በየሻ አካኮ ያሉትና ለዛሬ ምረቃ የደረሰውን ትምህርት ቤት የገነቡት ባለሀብቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሁለንትናዊ የሀገራችን ብልጽግና ለማረጋገጥ የግል ባለሀብቶች ድርሻ የላቀ መሆኑን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው ሀብቱ በባለቤትነት የባለሀብት ነው ቢባልም በመጠቀም ረገድ ሁላችንም ተጋሪዎች በመሆናችን የቀበሌው ህብረተሰብ ከባለሀብቶቹ ጎን በመቆም በመደገፍ ንብረቱን በመጠበቅና በመንከባከብ መጠቀም እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የሀገራችን የኢንቨስትመንት ፖሊስ ባለሀብቶቹ ኢንቨስት ስያደርጉ ህብረተሰቡ የሚፈልገውን ፍላጎትና የጎደለዉን ሟሟላት በመሆኑ ይህንን ተግባራዊ ያደረጉ ባለሀብቶች በዚሁ ቀበሌ መኖራቸውን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪ መሠረተ ልማት ሟሟላት ስራ የመንግስት ድርሻ ሆኖ ሳለ በመንገድ ስራም ሰፊ ርብርብ እያደረጉ ያሉት የግል ባለሀብቶች በመሆናቸው በዞኑ ስም ምስጋና አቀርበዋል።

የማሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን አዳሾ በበኩላቸው በማሻ ወረዳ ካሉት 27 ትምህርት ቤቶች መካከል በዛሬው ዕለት እየተመረቀ ያለው ትምህርት ቤት አንዱ ሲሆን መንግስት የትምህርት ስብራትን ለመጠገን የሚያደርገውን ጥረት የሚደግፍና ትምህርት ሚኒስተር ያወጣውን ደረጃ መሠረት አደርጎ የተገነባ ግንባታ መሆኑን ገልጸዋል።

የሻ አካኮ ህብረተሰብ ይህ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተገነባውን ትምህርት ቤት ደህንነቱን በመጠበቅ በመንከባከብ መጠቀም እንዳለባቸው አቶ መስፍን አዳሾ ተናግረዋል።

ከ1ኛ እስከ 4ኛ እና ከ5ኛ እስከ 8ኛ ደረጃ ያለውን ትምህርት ቤትን የገነቡት ሁለት ባለሀብቶች በሰጡት አስተያየት የተገነባው ትምህርት ቤት ለዚህ ተባባሪና ቅን ህብረተሰብ ቢያንስ እንጂ አይበዛም በማለት ደረጃውን የጠበቀና በጥራት የተገነባ በመሆኑ ለረዥም ጊዜ አገልግሎት እንድሰጥ መንከባከብ አለባቸው ብለዋል።

6 መቶ 21ሺህ ብር ለመንገድ ስራ ድጋፍ ማድረጋቸውን የተናገሩት ባለሀብቶቹ ትምህርት ቤቱን ሲገነቡ በአካባቢው ያለውን የትምህርት ቤት ችግር በማየት በመሆኑ በቀጣይ ለትምህምህርት ቤቱ መሟላት ያለውን ግብዓት እንደሚያሟሉ ተናግረው ህብረተሰቡ ብቻ ከጎናቸው እንድቆሙ ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቱ ተገንብተው በመመረቁ ህብረተሰቡ መደሰታቸውንና ባለሀብቶቹን በማመሰገን በቀጣይም ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ከባለሀብቶች ጎን በመሆን እንደሚሰሩ ተናግረው በመንግስት በኩል መደረግ ያለበት ድጋፎች ተጠናክሮ እንድቀጥል መጠየቁን የሸካ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

በዘንድሮ ዓመት ተሰርተው ይጠናቀቃል ተብሎ በክልል ደረጃ ዕቅድ ከተያዘው መንገዶች ከፈታፋ እስከ የሻ አካኮ ድረስ ያለው መንገድ በመሆኑ ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንድወጣ በመድረኩ ተገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *