






የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ”ለክልሉ ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላም ግንባታ የኃይማኖት ተቋማት ሚና”በሚል መሪ ቃል መንግሥትና የኃይማኖት ተቋማት የሰላም ፎረም ምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል።
በመድረኩ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ዘመናት በርካታ ፈተናዎችን ተቋቁማ አንደሀገር እንዲትቆምና በክልላችንም የነበሩ የተለያዩ ችግሮችን ተሻግረን በሀገር ደረጃ የተረጋጋና የተሻለ ሠላም ያለው ክልል እንዲንሆን የሀይማኖት ተቋማት የግንባር ቀደም ሚናቸውን ተወጥቷል ብለዋል።
የክልሉ ሠላምና የህዝቦች አንድነት እንዲጠበቅ ፣መተባባር፣መቻቻል እንዲሁም መተሳሰብ እንዲበዛ የኃይማኖት ተቋማት ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በክልሉ መንግስትና በቢሮ ስም አመስግነዋል።
ሠላም በሀገሪቱ ብሎም በክልላችን የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል ከየትኛው አጀንዳ በላይ በመሆኑ የኃይማኖት ተቋማት ለሰላም የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ያቀረቡት አቶ አንድነት እሰካሁን የተመዘገቡ ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆኖ የመጣውን ሰላም ለማጽናት አለመግባባቶችን በሰከነ መንገድ ለመፍታት በመቀራረብና በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፍትህና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች አማካሪ አቶ አክሊሉ ከበደ በበኩላቸው የማያግባቡ ጉዳዮችን በምክክር በመፍታት አንድነት መተሳሳብና የመቻቻል እሴትን ለማጎልበት በጋራ መስራት ይገባናል ብለለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሠላም ለሰው ልጆች ብቻም ሳይሆን ነፍስ ለላው ሁሉ አስፈላጊ በመሆኑ መንግስት በሠላም ግንባታ ላይ በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀው አስተማማኝና ዘላቂ ሠላምን ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ ባለፉት ጊዜያቶች ያደረጉትን ተሳትፎ በዘላቂነት እንደሚያጠናክሩም ገልጸዋል።
በመድረኩ በቢሮ ምክትልና የሰላም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ በአቶ ምትኩ ታምሩ በኩል ”ሁለንተናዊ ዘላቂ ሰላም ግንባታ የኃይማኖት ተቋማት ሚና”በሚል መሪ ቃል ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የተሰሩ እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችን የዳሰሰ ሰነድ ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል።
በፍቅር ከበደ
