በብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ማዕቀፍ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው::

Spread the love

በብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ማዕቀፍ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።

የሽግግር ፖሊሲ የባለሙያዎች ቡድን ላለፉት 8 ወራት የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በማወያየት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ረቂቅ አዘጋጅቶ ለፍትሕ ሚኒስቴር ማስረከቡ ይታወሳል።

በረቂቅ ፖሊሲውም በወንጀል ተጠያቂነት፣ የጊዜ ገደብ እና የሽግግር ፖሊሲውን ለመተግበር የሚያስፈልጉ አዳዲስ ተቋማት ተመላክተውበታል።

ሰብዓዊ መብት ተኮር ተግባር፣ ማንንም አለመጉዳት አውድ ተኮር አተገባበር እና ተጠያቂነት ረቂቅ ፖሊሲው የሚመራባቸው መርሆች መካከል መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክሮች ከተደረጉ በኋላም ፖሊሲው ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘላቂ ሰላም፣ እርቅ፣ የሕግ የበላይነት ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ የሚረጋገጥበት መደላድል መፍጠር የረቂቅ ፖሊሲው ዓላማዎች መሆናቸውም ተብራርቷል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *