






የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የ2015/16 ምርት ዘመን የበልግ ተግባር አፈፃፀም ግምገማና የ2016/17 ምርት ዘመን የበልግ የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በንቅናቄ መድረኩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት እንደ ክልል ተደራጅተን ወደ ስራ ከገባን ጊዜ ጀምሮ በተለይም በግብርና ስራዎቻችን ላይ በርካታ መሻሻሎችን እየታየ መምጣቱን ተናግረዋል።
ባለፉት ሁለት አመታት በርካታ ስራዎችን በጋራ በመሆን መከናወን በመቻቸላችን በምግብ እራሳችንን ከመቻሉም አልፎ አርሶ እና አርብቶ አደሮችን ምርት በማምረት ከራስ አልፎ ለወገን እንዲበቁ እና ጥሪት እንዲቋጥሩ መደረጉንም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡
በተለይም ክልላችን የሚታወቅበት ስራ በሰፊ የሚከናወን እንደመሆኑ መጠን በአማካይ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በዓመት ከ325 ሺህ 5 መቶ 85 ሄክታር መሬት በመሸፈን 10.3 ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን ገልፀዋል፡፡
በክልሉ በዘንድሮ በበልግ አዝመራ ከ3 መቶ 20 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት 11.9 ሚሊየን ምረት ለማግኘት እቅድ ተይዞ የሚሰራ መሆኑን አቶ ማስረሻ በላቸው ተናግረዋል፡፡
አቶ ማስረሻ የበልግ ወቅት ከፍተኛ ምርት የሚገኝበት በመሆኑ ያሉንን የተለያዩ አማራጮች በመጠቀም በተገቢው ለማከናወን ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡
የበልግ ወቅት ስራ ማለት በበልግ ወቅት የሚከናወኑ የእርሻ እና የእንስሳት እናዓሣ ሀብት ስራዎቻችን ጭምር ያጠቃልላልም ብለዋል፡፡
በበልግ ወቅት ወቅት ከሚሠራው ከአዝርዕት ስራ ባሻገር በዋናነት በተላይ በእንሰት ዘርፍ ስራ ላይ ሰፊ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
ከዚህም በሻገር ድርቅ በተደጋጋሚ በሚያጠማቻው በክልሉ በአንድ አካባቢዎች ለስራ ስር ሰብሎች ትኩረት እንደሚደረግና አንዱ ና ዋናኛ ተግባር የካሳቨ ምርት ማሻሻል በልዩ ትኩረት በንቅናቄ የሚንሰራ ይሆናል ብለዋል አቶ ማስረሻ፡፡
አሁን ባለው ደረጀ በክልሉ ከ147 ሺህ ሄክታር በላይ ማሣ በእንሰት ምርት መሸፈኑንና በተለያዩ አርሶ አደሮች እየለማ ያለ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
በዚህ በኩል የግብርና ተግባራትን በወቅቱ ከመስራት እስከ በክትትልና ድጋፍ ድረስ የሚታዩ የመጓተት አዝማሚያዎች ሊስተካከሉ የሚገባቸዉ ናቸዉ ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በዚህ በኩል የሚጠበቅባቸዉን እንዲወጡ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እንዲጠናከርም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ የክልል አመራሮች፣የዞን ዋና አስተዳደሪዎችና የግብርና መምሪያ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ሲሆን የክልሉ የ2015/16 ምርት ዘመን የበልግ ተግባር አፈፃፀም ሪፖርት በክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና በእርሻ ዘርፍ ኃላፊ በአቶ አሸናፊ ክንፈ እየቀረበ ነዉ።
በተከተል ወ/ሚካኤል
