ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ ከባድ የበልግ ዝናብ ልኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ::

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደጋማ አከባቢዎች ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ ከባድ የበልግ ዝናብ ልኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ለማ መሠለ አሳስበዋል።

የብሔራዊ ሜትሮዎሎጂ መረጃን ዋብ ያደረጉ ዶ/ር ለማ በክልሉ በተለይ በደጋማ አከባቢዎች በሚኖረው ከባድ የበልግ ዝናብ ጎርፍና ናዳ ልኖር እንደሚችልም አስረድተዋል።

በተለይ በክልሉ የመሬት መንሸራተት በተደጋጋሚ በሚከሰትባቸው አከባቢዎች፣ገደላማና ተዳፋት አከባቢዎች ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸውም አንስተዋል።

ከባድ የበልግ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይም ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብሎችን በጊዜ መሰብሰብ እንዳለባቸዉም ጠቁመዋል።

የበልግ ዝናብ ከባድ ሊሆን ስለሚችል ህብረተሰቡ ህፃናትንና ከብቶችን በጊዜ ወደ ቤት ማስገባት እንደሚገባና ዝናብ ከጀመረ በኋላም እስኪያቆም ድረስ እንቅስቃሴ ከማድረግ መቆጠብ ይገባልም ብለዋል።

ህብረተሰቡ የጎርፍ መፍሰሻ ቦታዎችን ማዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ጥንቃቄዎችን ማድረግ እንደሚገባም ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *