ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከኢቢሲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ዋና ስራ-አስፈፃሚና ከሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በክልሉና በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መካከል ያለውን ግንኝነት ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።

ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ኢቢሲ ህዝብና መንግሥትን በማቀራረብ እንዲሁም ከህዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ በማስተናገድ የጀመረው እንቅስቃሴ የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ አንኳር በሆኑ ክልላዊ ጉዳዮች በዜናና ፕሮግራም የሚሰጠውን ሽፋን እንዲያሳድግ ጠይቀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው የመረጃ ጥራትና ተደራሽነት ለማስፋት ኢቢሲ በክልሉ የማሰራጫ ማዕከል እንዲከፍት፣ቋሚ ሪፖርተር እንዲመድብና የክልሉ መንግሥት የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋም የጀመረውን ተግባር እንዲደግፍ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ-አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በበኩላቸው በክልሉ የመረጃ ተደራሽነት ለማሳደግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወኪል ሪፖርተር በመመደብ ዜናና ፕሮግራም በማምረት ሽፋን ለመስጠት ተቋሙ ቁርጠኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮርፖሬሽኑ የክልሉ መንግሥት የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋም የጀመረውን እንቅስቃሴ በቴክኖሎጂ ሽግግርና ሰው ሀብት እንደሚደግፉ የገለጹት ዋና ስራ-አስፈፃሚው በቀጣይ የቀጥታ ስርጭትን ጨምሮ ስቱዲዮ በመገንባት በዜናና ፕሮግራም ከክልሉ መንግሥት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል።

በክልሉ ለኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በዜና ዝግጅትና ይዘት ማበልጸግ ዙሪያ የክህሎትና ቴክኒክ ስልጠና በመስጠት ለማብቃት ተቋሙ ቁርጠኛ አቁም እንዳለው ዋና ስራ-አስፈጻሚው ጨምሮ ገልጸዋል።

የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ በበኩላቸው ኢቢሲ ከክልሉ መንግሥት ጋር ያለውን ግኑኝነት ለማጠናከር መወሰኑ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው ተቋሙ በጊዜያዊነት ወክል ሪፖርተር በመመደብ ለመስራት ለጀመረው እንቅስቃሴ አቅም በፈቀደው ሁሉ ቢሮው እንደሚደግፍ ተናግረዋል።

በውይይቱ የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የሥራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *