“ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና!”

Spread the love

“ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ አባላት ኮንፈረንስ ከመሠረታዊ ድርጅት እስከ ክልል ከመጋቢት 8-14 /2016 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።

በክልል በሁሉም ዞን ፣ወረዳ ፣ከተማ እና ቀበሌ /መሠረታዊ ድርጅት እንዲሁም በክልል ማዕከል የማጠቃለያ ፣ የተሳካ፣ ደማቅ እና በዓይነቱ ልዩ የሆነ የአባላት ኮንፈረንስ ለማድረግ የቅድመ-ዝግጅት ስራ የተሰራ ይገኛል።

ፓርቲያችን በስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ለህዝብ ቃል በገባው መሠረት ባለፉት ሁለት አመት ተከል በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ስኬቶችን መመዝገቡን ችሏል ። እያስመዘገበም ነው።

በተለይ በግብርና ፣በአምራች ኢንዱስትሪ ፣በማዕድን፣በቱሪዝም ፣በአረንጓዴ አሻራ እንዲሁም በመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና በመልከሠም አስተዳደር በርካታ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል።

በቀጣይ ቀሪ የምርጫ ዓመታት ፓርቲያችን ለህዝባችን በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ፋይዳ ያላቸውን ስራዎችን በመስራት የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ርብርብ እያደረገ ይገኛል።

እንዲሁም ፓርቲያችን በማኒፌስቶው ያስቀመጣቸውን የግማሽ የምርጫ ዘመን አፈጻጸም በየዘርፉ የተቀዱና የተለዩ የማሳኪያ መንገዶችን በፖለቲካና ዴሞክራሲ፣ በሰላም ግንባታ ፣በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በውጭ ግንኙነት የተገኙ ውጤቶችን ፣ያጋጠሙ ፈተናዎች እና የተወሰዱ የፖሊሲ እርምጃዎችን መሠረት በማድረግ በቀሪ የምርጫ ዘመን ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ያስቀምጣል።

የኮንፈረንሱን አላማና የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት አመራርና አባሉ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ፓርቲዉ ጥሪውን ያቀርባል።

“ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና!!!”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *