





ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነ-ስርዓት ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል።
በሽልማቱ የከበሩት ተቋማት የግብርና ሚኒስቴር/በስንዴ ልማት ፕሮግራም/፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መሆናቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
