









የአስተዳደር ሥራን ወደ ሕዝብ ለማቅረብ የቀበሌዎች መጠናከር ወሳኝ ነው። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በየአካባቢው ለሕዝብ ቅርብ የሆነ አስተዳደር ለመፍጠር (power devolution) ጥረት እያደረገ ነው። ከዚህ አንጻር በአምቦ ወረዳ የአንድ ቀበሌ እንቅስቃሴ በጉብኝት ወቅት ታይቷል። በዚህ ቀበሌን የማብቃት ተግባር በክልሉ 7342 ቀበሌዎች ተደራጅተዋል። 50,000 የሰው ኃይል ተመድቦላቸዋል።
ከዚህ ቀደም በወረዳዎች ተማክለው የነበሩ ሞያዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች በቀበሌ ደረጃ በተገቢው የሰው ኃይል እየተሰጡ ይገኛሉ።
ከዚህ በተጨማሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የወንጪ ደንዲ ኤኮ ሎጅ አካል የሆነው የደንዲ ክፍል ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል። የሥራው የሲቪል ግንባታ ሥራዎች ምዕራፍ ተጠናቆ አሁን የማጠናቀቂያ ሥራዎች በመሠራት ላይ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
