





የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 የ6 ወር እቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ቀሪ ወራት ዕቅድ ዙሪያ በቦንጋ ከተማ እየመከረ ይገኛል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ እንደተናገሩት
በክልላችን የጸጥታ ስራዉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መቶ ከቀዉስ ወደ አንጻራዊ ሰላም መሸጋገር ችለናል ብለዋል።
ሰላምን ባረጋገጥንባቸዉ አካባቢዎችም ሰላምን የማጽናት ስራዎችም ተጠናክረዉ እንደቀጠሉም ጠቁመዋል።
ከተለያዩ አጎራባች ዞኖችና ክልሎች ጋር ያለዉን ግንኙነት የማጠናከር ስራ ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑንም ገልጸዋል።
አቶ አንድነት በወሳኝ ኩነት ዘርፍ በኩልም ሽፋንን ለማሳደግና ጥራት ያለዉ መረጃ በመመዝገብ የተሻለ ስራ መከናወኑን ገልጸዋል።
በመድረኩ በወሳኝ ኩነት ዘርፍ የ2017 በጅት አመት የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም ረፖርት በክልሉ ጸጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊና የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደነቀ ቀርባል።
በሪፖርቱም ወሳኝ ኩነት ምዝገባን ለማጠናከር ስልጠና በመስጠት የአቅም የመገንባት እና ዘርፉን ማዘመን ላይ ትኩረት ተደርጎ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
አቶ ሰለሞን በቀጣይ በወሳኝ ኩነት ምዝገባ 37ሺ የሚሆኑ ወደ ድጂታል ምዝገባ ይገባሉ ተብሎ የታቀደ ሲሆን በበጀት አመቱ 8597 ወደ ድጂታል ምዝገባ መግባታቸዉን ሪፖርቱ አመላክቷል።
በመድረኩ በወሳኝ ኩነት ዘርፍ የግንዛቤ ሰነድ እና የወሳኝ ኩነት ረቂቅ መመሪያ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ እንደተገለጸዉ ወሳኝ ኩነት በአንድ ሰዉ ላይ ከልደት እስከ ሞት የሚከሰት ተፈጥሯዊና ማህበራዊ ክስተት ላይ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የተሳካ እንዲሆን የመንግስት ብቻ ሳይሆን ሁሉም የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ርብርብ ወሳኝ መሆኑንም በሰነዱ ተጠቁሟል።
በጸሀይ በላቸዉ
